የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ አዲስ የተመደቡ ዋናና ም/ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከዋና ቢሮ፣ ከባ/ዳ ጀኔራል ፍሌክሴብልና ፋውንደሪ እና ከባ/ዳ ከትራንስፎርመር ፋብሪካ የስራ መሪዎች ጋር በ16/08/2016 ዓ.ም ውይይት አደረጉ፡፡

የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪና ማሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኢንተርፕራይዝ አዲስ የተመደቡ ዋናና ም/ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከዋና ቢሮ፣ ከባ/ዳ ጀኔራል ፍሌክሴብልና ፋውንደሪ እና ከባ/ዳ ከትራንስፎርመር ፋብሪካ የስራ መሪዎች ጋር በ16/08/2016 ዓ.ም ውይይት አደረጉ፡፡ በውይይቱ ኢንተርፕራይዙ በአመራር ደረጃ የገጠመውን ችግር በተመለከተ ሰፊ ምክክር ተደርጓል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎችም አሉ የሚሎቸውን ችግሮች እንዲያነሱ ተደርጓል፡፡
አዲሶቹ አመራሮችም በኢንተርፕራይዙን ነባር አመራሮች የተሰሩ ጥሩ ስራዎች ቢኖሩም በመምራት በኩል በርከት ያሉ ችግሮች እንደነበሩ ከውይይቱ ለመረዳት እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡ በውይይቱም በአጠቃላይ አመራሩ የመምራት ችግር ምክንያት ኢንተርፕራይዙ በብድር ጫና ውስጥ እንዳለ፣ ለተደጋጋሚ ኪሳራ እንደተጋለጠ፣ በመንግስት፣ በውስጥና በውጪ ደንበኞቹ ዘንድ የእርካታ መጠኑ ዝቅተኛ እንደሆነ መግባበት ተፈጥሮል፡፡ በመጨረሻም የኢንተርፕራይዙ አዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘላለም በለይ ኢንተርፕራይዙን በቀጣይ ከችግር እንዲወጣ በጋራ መምራት እንደሚያስፈልግ የሠራተኛው፣ የመካከለኛ እና የከፍተኛ አመራሩ ትስስርና እንቅስቃሴ መኖር እንዳለበት ለዚህም እንደሚሰሩ አስረድተዋል፡፡ እንዲሁም ከመሪዎች የሚጠበቀውን አና መሪዎች ማወቅ የሚገባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ ያዘጋጁትን ፁሑፍ በማቅረብ እና ለቀጣይ ስራ በማነሳሳት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም

Views: 7

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top